Mahibere Kidusan Coordinating Center in North America logo

Mahibere Kidusan Coordinating Center in North America

Mahibere Kidusan in the USA is a nonprofit religious or spiritual organization. It is based in Silver Spring, MD. It received its nonprofit status in 2004.

16
DonateStart a fundraiser
Silver Spring, MD
Mid-sized organization
eotcmk.org
A 501(c)(3) nonprofit, EIN 84-1600968

Fundraisers

Feed fundraiser card link to “ግንቦትን ለግቢ ጉባኤያችን!” ኑ! ሃይማኖት ከሳይንስ የማይጋጭበትን ትውልድ እንገንባ!
Mahibere Kidusan Coordinating Center in North America logo
Fundraiser by Gbi Gubayat coordination MK USA

“ግንቦትን ለግቢ ጉባኤያችን!” ኑ! ሃይማኖት ከሳይንስ የማይጋጭበትን ትውልድ እንገንባ!

ማኅበረ ቅዱሳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎችን በግቢ ጉባኤ ሰብስቦ እያስተባበረ እና እያስተማረ ይገኛል፡፡ ለዚህ አገልግሎት ሥርዓተ ትምህርትና መማሪያ መጻሕፍት በማዘጋጀት፣ መምህራንና አስተባባሪዎችን በመመደብ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር መማሪያ ቦታ በማመቻቸት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ሥርዓት እና ትውፊት ሲያስተምር ቆይቷል፣ በማስተማርም ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ አገልግሎት የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ከግቢ ጉባኤ ባገኙት መንፈሳዊ ትምህርት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከሚደርስባቸው ፡- ከዓለማዊነትና ሉላዊነት /Globalization/ አስተሳሰብ አሉታዊ ተጽእኖዎች፣**** ከኦርቶዶክሳዊነት እና ከኢትዮጵያዊነት ዕሴት ማፈንገጥ፣ ከማኅበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ተጽእኖ፣ ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ተጽእኖዎች እና ጫና እንዲሁም ከጎሣ ፖለቲካ አስተሳሰብ መንሰራፋትና መሰል አሉታዊ ተጽእኖዎች ተጠብቀው ይወጣሉ፡፡ የዚህን አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለማስፋት ማኅበረ ቅዱሳን ባደረገው ተቋማዊ ለውጥ መሠረት የተከለሰውን ሥርዓተ ትምህርት ለመተግበር የሚያስችሉ፡-     የግቢ ጉባኤያት የመምህራን ማፍርያና የቨርቹዋል ሥልጠና ማእከል ለማቋቋም ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፤ ተግባራዊም ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡ ይህ ለግቢ ጉባኤያት ብቁ እና በቂ መምህራን እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚጠቅም ሲሆን ለአራት ዓመታት ብር 140,000,000.00 በአንድ ዓመት ብር 35,000,000.00 የፕሮጀክት በጀት ተይዞለታል፡፡ አጠቃላይ በሳምንት 1852 የግቢ ጉባኤያት መርሐ ግብራት ወይም በዓመት አጠቃላይ 3704 የኮርስ ዓይነቶች ለግቢ ጉባኤያት ይሰጣሉ፡፡ ይህ ማለት ለአንድ መምህር የሥልጠና በጀት በዓመት 12,000.00 ሲሆን የአንድ መደበኛ መምህር ዓመታዊ ደመወዝ 300,000.00 ብር ይሆናል፡፡   2.       የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት፣ ትርጉም እና ኅትመት ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ በተከለሰው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት 14 የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት/ሞጁል/ ማዘጋጀት እና 14ቱንም በልዩ ልዩ ቋንቋዎች መተርጎም ነው፡፡   ለዚህ ፕሮጀክት የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ለማዘጋጀት እና ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለመተርጎም ብቻ ማሳተሚያን ሳይጨምር 2,500,000.00 ብር በጀት ተይዞለታል፡፡   የመማሪያ መጻሕፍቱን ኅትመት በተመለከተ ዐሥራ ሦስት መጻሕፍት በኦሮምኛ ቋንቋ ይተረጎማሉ፡፡ በዚህ መሠረት 27 ዓይነት መማሪያ መጻሕፍት ሲሆኑ አንዱ መጽሐፍ 10,000 ኮፒ ቢታተም 27ቱ መጻሕፍት 270,000 ኮፒ ይሆናሉ፡፡ አንድ መጽሐፍ 100 ብር ቢታተም በጠቅላላው 27,000,000.00 ብር ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም እናንተም በቡድንም ሆነ በግል በመሆን የአንድ ሠልጣኝ በጀት፣ የአንድ መምህር ዓመታዊ ደመወዝ ወይም አንድ መማሪያ መጽሐፍ በስማችሁ እንዲዘጋጅ ወይም እንዲታተም በማድረግ ድጋፍ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ****    
Raised
$220
Goal
$50,000
4 supporters
Donate
Feed fundraiser card link to A Call to Support the 7th Campus Ministries General Assembly
7th Annual Campus Ministry General Assembly

A Call to Support the 7th Campus Ministries General Assembly

EOTC Mahibere Kidusan USA Campus Ministry, a 501(c) non-profit, is hosting the 7th Campus Ministry General Assembly in Atlanta, GA, from  ** July 18 to **July 20, 2025.  This three-day event, organized by Atlanta Campus Ministry, aims to engage recent high school graduates, all college students, recent undergraduates, current undergraduates, and graduate students in spiritual discussions, worship, and fellowship.. Your donations will help us create a meaningful experience for students and support our ministry’s development. "Give, and it will be given to you. A good measure, pressed down, shaken together, and running over, will be poured into your lap. For with the measure you use, it will be measured to you.” May God bless your giving hands!
Raised
$1,004
Goal
$5,000
14 supporters
Donate

Donors

  • Misrak Demissie

    Egiziabher yistilin. May God bless your services! May God be the Grace and strength of the young believers of Ethiopian Orthodox Tewahedo Chruch, generation to generation, forever!

    1
  • Tegenne Geber

    ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ እየሰጠ ያለው አገልግሎት ተገቢና ወቅታዊ ነው:: የእግዚአብሔር ቃል "ለሚለምነን ሁሉ" እንድንሰጥ ያሳስበናል:: ማኅበሩ ታማኝ ተቋም በመሆኑ የምንሰጠው ስጦታ በቀጥታ ለተጎጂዎች የሚደርስ ስለሆነ ምእመናን ደስ እያለን በመስጠት ልንጠቀም ይገባል:: ብንችል ሌሎችንም እየጋበዝን ከበረከቱ እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል::

  • Tinsae Debele

    MK Campus Ministry is one of the gates to follow the true faith.

  • Aida Yemaneberhan

    ግቢ ጉባኤ ቤተክርስቲያኔን ማንነት ያሳውቀኝ፤ በኃይማኖቴ ጸንቼ እንድኖር ያደረገኝ ፤ ለአሁን ማንነቴ ምክንያት የሆነኝ ስለሆነ የኔ እድል ለሌሎች እንዲደርሳቸው ቤተክርስቲያንን የሚታደጉ ትውልድ ለማፍራት እግዚአብሔር ቢረዳኝ እድሜ እና ጤና እስከ ሰጠኝ የበኩሌን አስተዋጾ ለማድረግ ቃል እገባለሁ

    1
  • Tsion Melesse

    ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።
    እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም።
    እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል...

  • Andualem Shoro

    " እኛ በግዜው ማድረግ ያለብንን ከማድረግ በዘገየን ቁጥር የምናጣቸው ነገሮች የበዙ ይሆናሉ።" ዛሬ መርዳት ያለብንን ወገኖቻችንን ዛሬ ካልደረስንላቸው ነገ ካጣናቸው በኋላ ብንንቀሳቀስ የዘገየ ይሆናል። መጽሐፉም ያንተ ቀን ዛሬ ናት ነው የሚለውና ዛሬን ከዛሬም አሁንን እንጠቀምበት።