“ግንቦትን ለግቢ ጉባኤያችን!” ኑ! ሃይማኖት ከሳይንስ የማይጋጭበትን ትውልድ እንገንባ!
- Raised
- $220
- Goal
- $50,000
ማኅበረ ቅዱሳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎችን በግቢ ጉባኤ ሰብስቦ እያስተባበረ እና እያስተማረ ይገኛል፡፡ ለዚህ አገልግሎት ሥርዓተ ትምህርትና መማሪያ መጻሕፍት በማዘጋጀት፣ መምህራንና አስተባባሪዎችን በመመደብ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር መማሪያ ቦታ በማመቻቸት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ሥርዓት እና ትውፊት ሲያስተምር ቆይቷል፣ በማስተማርም ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ አገልግሎት የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ከግቢ ጉባኤ ባገኙት መንፈሳዊ ትምህርት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከሚደርስባቸው ፡-ከዓለማዊነትና ሉላዊነት /Globalization/ አስተሳሰብ አሉታዊ ተጽእኖዎች፣**** ከኦርቶዶክሳዊነት እና ከኢትዮጵያዊነት ዕሴት ማፈንገጥ፣ ከማኅበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ተጽእኖ፣ ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ተጽእኖዎች እና ጫና እንዲሁም ከጎሣ ፖለቲካ አስተሳሰብ መንሰራፋትና መሰል አሉታዊ ተጽእኖዎች ተጠብቀው ይወጣሉ፡፡
የዚህን አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለማስፋት ማኅበረ ቅዱሳን ባደረገው ተቋማዊ ለውጥ መሠረት የተከለሰውን ሥርዓተ ትምህርት ለመተግበር የሚያስችሉ፡-
የግቢ ጉባኤያት የመምህራን ማፍርያና የቨርቹዋል ሥልጠና ማእከል ለማቋቋም ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፤ ተግባራዊም ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡
ይህ ለግቢ ጉባኤያት ብቁ እና በቂ መምህራን እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚጠቅም ሲሆን ለአራት ዓመታት ብር 140,000,000.00 በአንድ ዓመት ብር 35,000,000.00 የፕሮጀክት በጀት ተይዞለታል፡፡
አጠቃላይ በሳምንት 1852 የግቢ ጉባኤያት መርሐ ግብራት ወይም በዓመት አጠቃላይ 3704 የኮርስ ዓይነቶች ለግቢ ጉባኤያት ይሰጣሉ፡፡ ይህ ማለት ለአንድ መምህር የሥልጠና በጀት በዓመት 12,000.00 ሲሆን የአንድ መደበኛ መምህር ዓመታዊ ደመወዝ 300,000.00 ብር ይሆናል፡፡
2. የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት፣ ትርጉም እና ኅትመት ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ በተከለሰው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት 14 የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት/ሞጁል/ ማዘጋጀት እና 14ቱንም በልዩ ልዩ ቋንቋዎች መተርጎም ነው፡፡
ለዚህ ፕሮጀክት የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ለማዘጋጀት እና ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለመተርጎም ብቻ ማሳተሚያን ሳይጨምር 2,500,000.00 ብር በጀት ተይዞለታል፡፡
የመማሪያ መጻሕፍቱን ኅትመት በተመለከተ ዐሥራ ሦስት መጻሕፍት በኦሮምኛ ቋንቋ ይተረጎማሉ፡፡ በዚህ መሠረት 27 ዓይነት መማሪያ መጻሕፍት ሲሆኑ አንዱ መጽሐፍ 10,000 ኮፒ ቢታተም 27ቱ መጻሕፍት 270,000 ኮፒ ይሆናሉ፡፡ አንድ መጽሐፍ 100 ብር ቢታተም በጠቅላላው 27,000,000.00 ብር ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም እናንተም በቡድንም ሆነ በግል በመሆን የአንድ ሠልጣኝ በጀት፣ የአንድ መምህር ዓመታዊ ደመወዝ ወይም አንድ መማሪያ መጽሐፍ በስማችሁ እንዲዘጋጅ ወይም እንዲታተም በማድረግ ድጋፍ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
****