Fundraisers
ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ መሳካትና ለሕልውናዋ የሚተጋ ትውልድ ከግቢ ጉባኤ በተሻለ ጥራት እናፍራ
ግቢ ጉባኤያት የአገልግሎታችን መሠረት ናቸው፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳን መመሥረት ምክንያት ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ የአገሪቱ መንግሥት ይከተለው በነበረው ርእዮተ ዓለም “እግዚአብሔር የለም” አስተሳሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ያየለበትና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ውስጥ መንሰራፋት ትውልዱን ከመንፈሳዊነት በማራቁ፣ እንዲሁም የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ተጽእኖን ለመከላከል ይደረግ የነበረውን የኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ውጤት ነው፡፡ ይህ ማለት ማኅበረ ቅዱሳን በ1984 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ደንብ ላይ ከተጠቀሱት ሓላፊነቶች ውስጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች በማኅበሩ ሥር አደራጅቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓትና ትውፊት እንዲማሩ በማድረግ ተተኪ የቤተ ክርስቲያን ትውልድን ማፍራት፣ የአጽራረ ቤተ ክርስቲናንን እንቅስቃሴን በመግታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙትን ወጣቶች በአርባ እና በሰማንያ ቀን ያገኙትን የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን አጽንተው እንዲይዙ ማድረግ ነው፡፡ ከወጡ በኋላም በተሠማሩበት የሥራ መስክ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ሀብታቸውን ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም አገልግሎት ላይ እንዲያውሉ ማብቃት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ 467፣ በውጭ አገራት 24 ግቢ ጉባኤያትን ያስተባብራል፣ ያስተምራል፣ ይከታተላል፣ በአባቶች ቡራኬ በአደራ መስቀል እያስመረቀ ይገኛል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮንም ለማሳካት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር በመግባት በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ እና በአገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ ንቁ ተሳታፊ ሆነው የድርሻቸውን እንዲወጡ ማኅበረ ቅዱሳን የሚጠበቅበትን ሓላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የአብነት ትምህርት በማስተማር ለክህነት ማዕረግ በማብቃት፣ ሴት የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በአካዳሚክ ትምህርታቸው፣ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲሁም በቀጣይ ኑሮአቸው ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ በማገዝ፣ ከጠረፋማ እና የአገልጋይ እጥረት ካለባቸው ቦታዎች ለመጡ ተማሪዎች አቅማቸውን ማሳደግ፣ ተተኪ አመራር እና መምህራን ማፍራት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ክህሎት እንዲለማመዱ፣ በአካዳሚክ ትምህርታቸው ከፉክክር ይልቅ መረዳዳት ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ውጤት የማምጣት ባሕል እንዲኖራቸው እና እንዲረዳዱ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የግቢ ጉባኤ ውጤቶች በዚህ አገልግሎት ብዙዎች፡- እንደ አንድ ክርስቲያን ራሳቸውን ከውስብስብ የዓለም ከባቢያዊ ሁኔታዎች እና ከግላዊ ፈተናዎች ወጥተው ማለትም፡- ከሴኪውላሪዝም (ከዓለማዊነት)፣ ከሱስ፣ ከዘረኝነት፣ ከግብረ ሰዶማዊነትና ከመሳሰሉት አስተሳሰቦች ርቀው በኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ እና ኑሮ ተቃኝተው እንዲኖሩ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል፣ እንደ ቤተሰብ መልካም አርአያነት ያለው ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ለማፍራት እንዲችሉ በማገዝ፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ተልእኮ መሳካት ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እና መሪዎችን ማፍራት፤ በዕውቀቱ/በሞያው/፣ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በጊዜው እንዲያገለግል ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ እንደ አገር በመልካም ሥነ ምግባር የታነጸ፣ ሙስናን የሚጸየፍ፣ ሞያውን አክብሮ የሚሠራ እና ያስተማረውን ማኅበረሰብ የሚክስ ትውልድ እንዲሆን ማድረግ ችሏል፡፡ ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ላይ እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ከግቢ ጉባኤያት እና ከተማሪዎች ብዛት ጋር የማይጣጣም የመምህራን ችግር (በጥራትም በቁጥርም ማነስ) የመማሪያ እና የማሠልጠኛ ቦታዎች ከፍተኛ ችግር መኖሩ እና ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት እስከ 8 ኪሎ ሜትር የሚጓዙ ተማሪዎች መኖራቸው (ምሳሌ፡- ቀብሪደሃር እና ወራቤ)፣ የዓለም አቀፍ ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች የሚያሳድሩት ጫና፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዙሪያ የወጡ ሕጎች አተረጓጎም በየከፍተኛ ትምሀርት ተቋማቱ የሚያሳድረው ጫና፣ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጫና እና ሌሎችም
በዚህ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ከላይ ያየናቸውን ችግሮች ለማስወገድና ውጤቶቶቻቸውን ለማስቀጠል፡- መደበኛ መምህራንን እና አስተባባሪዎችን መቅጠር እና ጥራት ያለው፣ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፣ የመምህራን ትምህርት ሥልጠና ተቋማትን መገንባት፣ ተከታታይነት ያላቸው የማስተማር ሥነ ዘዴዎችን (ፔዳጎጂ ሥልጠና መስጠት) የመማሪያ ቦታዎችን ለማመቻቻት፣ ቨርቱዋል የማስተማር ዘዴ ግብዓቶችን ለማሟላት (ላፕቶፕ፣ኤልሲዲ እና ፕሮጀክተር) ግቢ ጉባኤያትን በኃላፊነት የሚመሩ እና የሚያስተባብሩ መሪዎችን ከታች እስከ ላይ ማፍራት እና ማሰማራት ላይ ከፍተኛ ሥራ ይጠብቀናልና በግቢ ጉባኤያት ያለፋችሁ፣ አገልግሎቱን በቅርበት የምትረዱ፣ እንዲሁም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ድጋፍ ታደርጉ ተጋብዛችኋል፡፡ “ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ነገር ነው፡፡” (2ቆሮ.11፥28)
- Raised
- $920
- Goal
- $50,000
$1,200 Annual recurring total
5 supporters
Donateበደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም የነበሩ ግን የታጠፉ ጉባኤ ቤቶችን መልሰን እናቋቁም!
ቅዱስ ያሬድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ አምልኮዋ የምትጠቀምባቸው መጻሕፍትን ዜማ በመድረስ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመድረስ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉልህ ድርሻ ከአበረከቱት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መካከል አንድ ነው፡፡ የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በሰሜን ጎንደር በራስ ደጀን አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ገዳሙ ቅዱስ ያሬድ ጉባኤ ቤት መስርቶ ሊቃውንትን ካፈራባቸው ገዳማት አንዱ ነው። በቅርቡም የፕሮጀክቱ ጥናት በተከናወነበት ወቅት በገዳሙ ስልሳ (43 መነኮሳት እና 17 መነኮሳይያት)፣ 13 ዲያቆናት እና 5 ቀሳውስት ይገኛሉ፡፡ በገዳሙ ውስጥ 30 ተማሪዎች የአብነት ትምህርት ሲማሩ የነበሩ ቢሆንም በአካባቢው ባለው ችግር ምክንያት ገዳሙን ለቀው ወጥተዋል፡፡
ይህንን ታሪክ ጠብቆ ለማቆየት ደግሞ የገዳሙ መሠረታዊ ችግሮች ሊፈቱ ይገባል፡፡ በዚህ መሠረትም ማኅበረ ቅዱሳን ገዳሙን ለማጠናከር ከደባርቅ ከተማ አስተዳደር 1000 ካ.ሜ ለንግድ የሚሆን ቦታ የተረከበ ሲሆን በዚህም ቦታ ላይ ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ህንጻ ለመገንባት ጥናት አድርጓል።
ይህንን የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ሁለገብ የሕንጻ ፕሮጀክት በገንዘብ በመደገፍ
1 የገዳሙን መንፈሳዊ አገልግሎት በማጠናከር ማኅበረ መነኮሳቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ለገዳሙ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በልመና ከማሟላት ይልቅ መንፈሳዊ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ፣
2 የአብነት ተማሪዎቹን እና መምህራኑን የምግብ እና የአልባሳት ችግሮችን በመፍታት ለቤተ ክርስቲያን ተተኪ ለማፍራት፣
3 የገዳማውያንን ፍልሰት በማስቀረት ገዳሙ እንዳይፈታና ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር ለማድረግ
የበኩልዎን የልጅነት ድርሻ እንዲወጡ በእንተ ስማ ለማርያም ስለ እመብርሃን እያልን እንጠይቃለን። ስለሚያደርጉት ድጋፍ ሁሉ የቅዱሳን አምላክ አብዝቶ ይስጥልን።
- Raised
- $25,800
- Goal
- $100,000
5 supporters
Donate